Fana: At a Speed of Life!

ለብሔራዊ ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልጠና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ወጣቶች ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ለብሔራዊ ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልጠና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ወጣቶች ከሰላም ሚኒስቴር በጎ ፍቃድ ፕሮጀክት አመራረሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በመድረኩ የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር ጀነራል ወይዘሮ አስማ ረዲ እና የሚኒስትር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ዮሐንስ አመነ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ተሳታፊ ወጣቶችም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት በቂ ምላሽና ማብራሪያ በውይይቱ ወቅት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በተጨማሪም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሬስ የሱፍ÷ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈው በቀጣይም ወጣቶቹ በሚኖራቸው ጊዜ ለሚያስፈልጓቸውን ሁሉ ከጎናቸው በመሆን እንደሚደግፏቸው ገልጸዋል፡፡
የአመራር ልኡካን ቡድኑ የወጣቶችን የአመጋገብ ስርዓታቸውን፣ የአካባቢ ንጽህና ሁኔታና የመኝታ ክፍሎቻቸውን ጎብኝተዋል፡፡
በቀጣይ ቀናትም ስለቆይታቸው ጊዜ እና የስራ ክንውኖች ገለጻ እንደሚደረግላቸውና ወደ ስልጠናው እንደሚገቡ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.