ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የካፒቶል ሂሉን ሁከት አነሳስተዋል በሚል እንዲከሰሱ ተወሰነ

By Tibebu Kebede

January 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካፒቶል ሂሉን ሁከት አነሳስተዋል በሚል እንዲከሰሱ ውሳኔ ተላለፈ።

የህግ መምሪያ ምክር ቤት እንደራሴዎች ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን የካፒቶል ሂል ሁከት በመምራት እንዲከሰሱ በአብላጫ ድምጽ ወስነዋል፡፡

እንደራሴዎቹ 232 በ197 በሆነ አብላጫ ድምፅ ነው ፕሬዚዳንቱ እንዲከሰሱ የወሰኑት፡፡

ትራምፕ ጆ ባይደን ያሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስና ደጋፊዎቻቸውን ለአመፅ በማነሳሳትም በተወካዮች ምክር ቤት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ትራምፕ ስልጣን ላይ እያሉ ሁለት ጊዜ እንዲከሰሱ የተወሰነባቸው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል ነው የተባለው፡፡

ባለፈው የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ ጥቅምት 20 ቀን በይፋ በዓለ ሲመታቸው ይካሄዳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!