የሀገር ውስጥ ዜና

ቱርክ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

By Feven Bishaw

January 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የተመራ ልዑክ በቱርክ ኢስታንቡል ከቱርክ ቢዝነስ ካውንስልና በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንት መስኮች ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ የባንክ ዋስትና አሰጣጥ፣ የህግ ማስከበር ስራዎችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያሉ ክፍተቶች በተሳታፊዎች ተነስተው ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በቱርክ በኩልም በቀጣይ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የበለጠ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መግለፃቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡