Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኦስትሪያው አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኦስትሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ሻለንበርግ ጋር ተወያዩ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በትግራይ ክልል በተካሄደው ህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በህዳሴ ግድብ እና በኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይም ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅትም አቶ ደመቀ በህወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ መንግስት ህግ ወደማስከበር እርምጃ መግባቱን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የተካሄደው ህግ የማስከበር እርምጃም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቋል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም አቶ ደመቀ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ግድቡን በራሷ ወጪ እየገነባች መሆኑን አውስተዋል፡፡

ከግድቡ ጋር በተያያዘም በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ አካሄድ መከተሏንና በግድቡ ዙሪያ ያሉ ልዩነቶችን ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ በሚል እሳቤ በአፍሪካ ህብረት በኩል ለመፍታት እየሞከረች መሆኗንም ገልጸዋል፡፡

የኦስትሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ሻለንበርግ በበኩላቸው መንግስት በትግራይ ክልል የተካሄደው ህግ ማስከበር ዘመቻ በጥንቃቄ እና በአጭር ጊዜ ማጠናቀቁን አድንቀዋል።

በብስራት መለሰ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.