Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ መቀመጫውን ታንዛኒያ ካደረገው የአፍሪካ ማዕድን እና ጂኦ ሳይንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ መቀመጫውን ታንዛኒያ ዳሬሰላም ካደረገው የአፍሪካ ማዕድን እና ጂኦ ሳይንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢብራሂም ሻዳድ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ኢትዮጵያ ለማዕከሉ ያላትን ድጋፍ እና ከማዕከሉ ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን ያላትን ፍላጎት አምባሳደሩ የገለጹ ሲሆን በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይም ለዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ አድርገዋል።
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ኢትዮጵያ የማዕከሉ መስራች አባል ሃገር መሆኗን እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ማዕከሉን የመምራት እድል አግኝተው እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
በቀጣይም ኢትዮጵያ ለማዕከሉ ያላትን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል።
እንዲሁም በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተሰጣቸው ማብራሪያ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የሱዳን እና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ከመንግስታት ያለፈ እና በህዝብ ለህዝብ ትስስር የጠነከረ መሆኑን በማስታወስም በአሁኑ ወቅት የታየውን ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሁለቱን ሃገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው ማለታቸውን ከታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር ዮናስ ከውይይቱ ባሻገር የአፍሪካ ማዕድን እና ጂኦ ሳይንስ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.