Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የሲሚንቶ እጥረትን ለመፍታት በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወሰዱ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሲሚንቶ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል።
የፌደራል ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በክልሉ የሲሚንቶና የብረት ምርት አቅርቦት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የፌደራል ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮና የፌደራል አጋር አካላት እንዲሁም የሲሚንቶ ፋብሪካዎችና ነጋዴዎች ተገኝተዋል።
በውይይቱ የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትና የአሰራር ችግሮች መኖራቸውን ተሳታፊዎቹ አንስተዋል።
በተለይ ያለደረሰኝ መሸጥና መግዛት፣ የደላላ ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በሀገር አቀፍ የሲሚንቶ ስርጭት ኢ-ፍትሐዊነት በችግር ተነስተዋል ።
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ተዋቸው ወርቁ ÷ የሲሚንቶ አቅርቦትና የዋጋ ንረት መኖሩን ገልጸዋል።
ለዚህም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅም አለማምረትና ምርቱን በፍትሃዊነት ያለማሰራጨት፣ ከነጋዴዎች ስግብግብነት እና የመንግስት ክትትልና ቁጥጥር አናሳ መሆን በምክንያትነት አቅርበዋል።
የፌደራል ኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብአቶች ኢንዱስትሪ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሀላላ በበኩላቸው÷ የክልሉን የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ የአባይ ተፋሰስ ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ግብአት ክምችት እንዳለው የገለፁት አቶ ሳሙኤል ÷ በዚሁ አካባቢ የአባይ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ወደስራ እንዲገባ ተደርጓል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ለማፋጠን የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ለመፍታት በመንግሥት የ30 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደርጎለታልም ነው ያሉት።
በክልሉን ባለው ሰፊ የሲሚንቶ ግብአት አቅም ልክ ለማምረት በሰሜን ሸዋ ዞን በጃማ ቤልት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን አቶ ሳሙኤል አስረድተዋል።
በናትናኤል ጥጋቡ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.