Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት  በአዲስ አበባ ያካሂዳሉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት  ታህሳስ 29 እና 30 ቀን 2012  ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳሉ፡፡

ውይይቱ የሶስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በተገኙበት እንደሚካሄድ ነው የተነገረው፡፡

ይህ የቴክኒክ ስብሰባ በግድቡ ውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ፣ ካይሮ ፣ ካርቱም እንዲሁም በዋሽንግተን መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.