Fana: At a Speed of Life!

2 ሺህ 525 ተተኳሽ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ተደብቆ ሲጓጓዝ የነበረ 2 ሺህ 525 ተተኳሽ የክላሽ ጥይት መያዙን የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታወቀ።
የቅርንጫፉ የደንበኞች ትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ አሳምነው አዳነ እንደገለጹት ተተኳሽ ጥይቱ የተያዘው ትናንት ሌሊት በወልዲያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ነው።
ጥይቱ ከአላማጣ ወደ ባህር ዳር በመጓጓዝ ላይ በነበረ አይሱዚ የጭነት ተሽከረካሪ በሽንኩርት ውስጥ ተደብቆ ሊያልፍ ሲል በፍተሻ መገኘቱን ተናግረዋል።
ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በተደረገ ትብብር አሽከርካሪውን ጨምሮ ሦስት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.