የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የውስጥ ኦዲተሮች የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ደንብ አፀደቁ

By Tibebu Kebede

January 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የውስጥ ኦዲተር ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ደንቡ እንዲፀድ ተደርጓል፡፡

የውስጥ ኦዲተሮች የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ደንብ የውስጥ ኦዲት ቁጥጥር ስርዓቱን ለማጠናከር እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት የበላይ ኃላፊዎች አስተማማኝና በመረጃ የተደገፈ ሙያዊ አስተያየት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የማኔጅመንት ድጋፍ ሥራ አመራር ዳይሬክተር ጀነራል አቶ መብራቱ ካሣ በውይይቱ ላይ÷ የመተዳደሪያ ደንቡ የሰላም ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ በአዋጅ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነቶች በብቃት ለማሳካትና የተመደበላቸውን ውስን ሃብት በአግባቡ መጠቀማቸውን ለመከታተል ከፍተኛ ዕገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የኦዲት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ዘነበ በበኩላቸው÷ መተዳደሪያ ደንቡ የሰላም ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ኦዲተሮች ተናበው እንዲሰሩና አሰራራቸው የህግ ማዕቀፍን የተከተለ ለማደረግ አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!