A demonstrator gives the victory sign during a protest, in Khartoum, Sudan, Saturday, Dec. 19, 2020. Protests in Sudan’s capital and across the country are demanding a faster pace to democratic reforms, in demonstrations that are marking the two-year anniversary of the uprising that led to the military’s ouster of strongman Omar al-Bashir. (AP Photo/Marwan Ali)

ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሱዳናውያን ተቃዋሚዎች ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፀምባቸው እስር ቤቶች እንዲዘጉ ተቃውሞ አሰሙ

By Tibebu Kebede

January 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ ሱዳናውያን ሁሉም ህገ ወጥ እስር ቤቶች እንዲዘጉ በካርቱም በተቃውሞ ሰልፍ አሰምተዋል።

ሱዳናውያኑ ተቃውሟቸውን ያሰሙት የሀገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል አንድን ግለሰብ በማሰቃየት እና በመግደል ክስ ከቀረበበት በኋላ ነው።

የሀገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ዘመነ መንግስት በዳርፉር  የጦር ወንጀል ፈፅሟል የሚል ክስ ይቀርብበታል።

ባለፈው ወር ባሃ ኢል ዲን ኖሪ የተባለ ወጣት በአንድ ቡና መጠጫ በተቀመጠበት ወቅት በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በቁጥጥር ስራ ውሎ ህይወቱ ካለፈ በኋላ የዚህ ሀይል ሃላፊነት ላይ ብዙ ክርክር ሲደረግ ቆይቷል።

በካርቱም ተቃውሟቸውን ያሰሙት ሱዳናውያኑም በሀይል ሰው ማጥፋት አይገባም ሲሉ ድምፃቸውን ማሰማታቸውን ኤቢሲ ኤፒን ዋቢ አድርጓ ዘግቧል።

ይህን ተቃውሞ የጠራው ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አል በሽር ከስልጣን እንዲወገዱ የአንበሳውን ድርሻ ከተወጡት መካከል የሆነው የሱዳን ሙያተኞች ማህበር ነው።

የማህበሩ አባል የሆኑት አማር አል ባቄር የተቃውሞው አላማ ህገ ወጥ የእስር ማእከላት እንዲዘጉ እና ፖሊስ ብቻ በህጉ መሰረት ሰዎችን እንዲያስር ለመጠየቅ ነው ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!