የሀገር ውስጥ ዜና

በግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን የተመራ ልዑክ ጂቡቲ ገባ

By Tibebu Kebede

January 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጂቡቲ ገብቷል።

ልዑኩ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ ከጂቡቲ የግብርና ሚኒስትርና ከጂቡቲ የወደብ አካባቢ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

ውይይቱ በዋናነት ከጂቡቲ ወደ ሃገር ቤት በሚገባው የማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር የትራንስፖርትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኩራልም ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!