የሀገር ውስጥ ዜና

የምክንያታዊ ወጣት የውይይትና የሙግት መድረክ በነገው እለት በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ይካሄዳል

By Tibebu Kebede

January 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክንያታዊ እና በእውቀት ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ ያላቸው ወጣት ምሁራንን ለመፍጠር በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ያለው የምክንያታዊ ወጣት የውይይትና የሙግት መድረክ እንደቀጠለ ይገኛል።

በብልጽግና ወጣቶች ሊግ እየተሰናዳ የሚገኘው ይህ መድረክ በነገው እለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ሆቴል እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በትሪያንግል ሆቴል ይካሄዳል።

በመድረኩ ከአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ወጣት ምሁራን ይታደማሉ።

ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚሰሩ ወጣት ምሁራን ይሳተፋሉ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!