የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግር ተግዳሮቶችን በተመለከተ በባህርዳር ከተማ ውይይት እየተደረገ ነው

By Tibebu Kebede

January 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግር ተግዳሮቶችን በተመለከተ በባህርዳር ከተማ ውይይት እየተደረገ ነው።

በውይይቱ ላይ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የህዝብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ውይይቱ በትናንትናው እለት ከተጀመረው የምክክር መድረክ የቀጠለ ነው።

በዛሬው እለትም የሽግግር ፅንሰ ሀሳብን ጨምሮ በኢትዮጵያ የተደረጉ የሽግግር ሙከራዎች እና አሁን ላይ ያለው ሽግግር እንደ ሀገርና እንደ ህዝብ ያለውን መልካም አጋጣሚዎች በተመለከተ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል ።

በትዝታ ደሳለኝ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!