የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ትምህርት ለማስቀጠል ስራዎች እየተሰሩ ነው

By Tibebu Kebede

January 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ሲኒቨርስቲዎችን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በክልሉ የተደረገውን የህግ ማስከበር ተከትሎ መቐለና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ያስመረቁ ሲሆን የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።

በቀጣይም የመቐለና አዲግራት ነባር ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር በሚቻልበት ሁኔታና ለተቋማቱ መደረግ ባለባቸው ድጋፎች ላይ ውይይትና የስራ ክፍፍል ተደርጓል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በህግ ማስከበር ወቅት የደረሰውን ጉዳት ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ ከተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!