የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ወሎ ዞን የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ በተንታ ወረዳ ተጀመረ

By Tibebu Kebede

January 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ወሎ ዞን የ2013 ዓ.ም የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተንታ ወረዳ ተጀመረ።

የወረዳው አርሶ አደሮች እንዳሉት በየዓመቱ የሚያከናውኑት የተቀናጀ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ የተራቆቱ አካባቢዎችን ወደ ልምላሜ በመቀየር ለግብርና ምርታማነታቸው ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

የተፈጥሮ ሐብት ልማት ሥራውን በሥነ ህይወታዊ ዘዴ በማጠናከር ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውንም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በየዓመቱ በዘመቻ የሚተገበረው የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ ዘላቂ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲሆን በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

መንግሥት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችን ከማቅረብ ጀምሮ አስፈላጊ የግብርና ግብዓቶችን ለማሟላት ጥረት እያደረገ ነው ማለታቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!