የሀገር ውስጥ ዜና

የምክንያታዊ ወጣት የውይይትና የሙግት መድረክ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

January 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምክንያታዊ ወጣት የውይይትና የሙግት መድረክ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ ከከተሞቹ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ምሁራን ወጣቶች እየተሳተፋበት ሲሆን የሀገረ መንግስት ግንባታና የወጣቱ ሚና በሚል ርዕስ የተሰናዳ መሆኑ በመድረኮቹ ተገልጿል።

በመድረኩ ምሁራን ወጣቶች ምክንያታዊ ሆነው የሃገር ግንባታ ላይ አሻራቸውን ለማሳረፍ ምክንያታዊ እና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሙግት እያደረጉ ይገኛሉ።

በብልጽግና ወጣቶች ሊግ እየተሰናዳ የሚገኘውና በመላ ሃገሪቱ እየተካሄደ ባለው መድረክ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቡ ውይይት እየደተረገበት ይገኛል፡፡

በመድረኩ የዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ምሁራን፣ የዓለም አቀፍ ድርጅት ሰራተኞች፣ ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እንዲሁም በርካታ የከተማዋ ወጣቶች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!