ኢ/ር ታከለ ኡማ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በክረምት በጎፈቃድ መርሃ ግብር ቤታቸው የታደሰላቸው እናቶችን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በክረምት በጎፈቃድ መርሃ ግብር ቤታቸው የታደሰላቸው እናቶች ቤት ቆይታ አድርገዋል።
በጉብኝቱ ከምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ በተጨማሪ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የከተማ አስተዳደሩ ባሳለፍነው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር በመዲናዋ ውስጥ ለሚገኙ 1ሺህ 573 ለሚሆኑ አረጋዊያን የመኖሪያ ቤት እድሳት ማከናወኑ ይታወሳል።