ስፓርት

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆነ

By Tibebu Kebede

January 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጁቬንትሱ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 760 ጎሎችን በማስቆጠር በእግር ኳስ ታሪክ የዓለማችን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ቻለ፡፡

ሮናልዶ ትናንት ምሽት በጣሊያን ሱፐር ካፕ ናፖሊ ላይ ጎል ማስቆጠሩን ተከትሎ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ክብረ ወሰን ባለቤት ሆኗል፡፡

ትናንት ምሽት ያስቆጠረው ጎል 760ኛ ጎሉ ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም የኦስትሪያው ዮሴፍ ቢካን ያስቆጠረውን 759 ጎልን አሻሽሎታል፡፡

ፖርቹጋላዊው አጥቂ በቅርቡ የብራዚላዊውን ፔሌ የ757 ጎል ክብረ ወሰን መጋራቱ ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!