የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

By Tibebu Kebede

January 07, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት ታህሳስ 29 እና 30 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳሉ።

ውይይቱ የሶስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በተገኙበት እንደሚካሄድ ነው የተነገረው።