ቴክ

ጎግል የመረጃ ማፈላለጊያ ፕሮግራሙን በአውስትራሊያ ሊያቋርጥ እንደሚችል አስጠነቀቀ

By Meseret Awoke

January 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎግል የመረጃ ማፈላለጊያ ፕሮግራሙን በአውስትራሊያ ሊያቋርጥ እንደሚችል ማስጠንቀቁ ተሰምቷል፡፡

ኩባንያ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው በአውስትራሊያ ከመረጃ እና ዜና ጋር በተያያዘ አዲስ ህግ ሊተዋወቅ መሆኑን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በአውስትራሊያ ጎግልን ጨምሮ ፌስቡክ እና መሰል ኩባንያዎች የሚዲያ አውታሮች ለሚያጋሩት ዜና ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚጠይቅ አዲስ ህግ እየወጣ ነው፡፡

አዲሱ ህግ የዜናው ባለቤት ነው ለተባለው ተቋም ወይም ግለሰብ ላጋራበት ኩባንያዎቹ ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገድዳል፡፡

ይህ መሆኑ ደግሞ እንደ ጎግል ያሉ ኩባንያዎችን አስቆጥቷል፡፡

ህጎቹ ጠንከር ያሉ እና በማህበረሰቡ የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ ችግር ይፈጥራሉ በሚልም ተቃውሞታል፡፡

በአውስትራሊያ የጎግል ሥራ አስኪያጅ ሜል ሲልቫ ህጎቹ የማይሰሩ ናቸው ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

ይተገበራል በተባለው አዲስ የክፍያ ህግ ላይ ስምምነት ካልደረሱም የጎግል መፈለጊያ በአውስትራሊያ ከማቆም ውጭ ምንም አማራጭ የለንም ነው ያሉት ስራ አስኪያጇ፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!