የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት ስድስት ወራት 135 አዳዲስ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል

By Tibebu Kebede

January 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት 135 አዳዲስ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽነት ከማረጋገጥ አኳያ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት 142 ሺህ 11 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል፡፡

የሃገሪቱን የኤሌክትሪክ ሽፋን ለማሳደግና ኤሌክትሪክን ለማዳረስ በተደረገ ጥረት 135 አዲስ የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎች የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓልም ነው ያለው፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በመንፈቅ ዓመቱ 9 ነጥብ 21 ቢሊየን ብር ማግኘቱንና አፈጻጸሙም 82 በመቶ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!