የሀገር ውስጥ ዜና

በወቅታዊ የዘይት ግብዓት ችግሮች ዙሪያ የንግድ ሚኒስቴር አምራቾችና አስመጭዎችን ጨምሮ በዘርፉ ያሉ አካላትን አወያየ

By Meseret Awoke

January 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በወቅታዊ የዘይት ግብዓት ችግሮች ዙሪያ የንግድ ሚኒስቴር አምራቾችና አስመጭዎችን ጨምሮ በዘርፉ ያሉ አካላትን አወያይቷል፡፡

ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የዘይት ዋጋ በገበያ ላይ በተከታታተይ የመጨመር ዝንባሌ ቢያሳይም፤ ከአንድ ወር ወዲህ ግን በስግብግብ ነጋዴዎች ምክንያት የዋጋ ንረቱ ጣሪያ መንካቱ ይገለጻል፡፡

መንግስት ችግሩን ለመቋቋም በበጀት ደጉሞ በተመረጡ አስመጪዎች ዋጋ ለማቅረብ ሙከራ ማድረጉን የገለጹት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዲኤታ እሸቴ አሰፋው ናቸው፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ ከቀረጥ ነጻ የፈሳሽ ዘይት እንዲገባ ቢደረግም፤ ከፍተኛ ትርፍ ማግበስበስ በሚፈልጉ ነጋዴዎች ምክንያት ህዝቡ ቅሬታ እያቀረበም ይገኛልም ብለዋል፡፡

የህገ- ወጥ ግብይት እና አብዛኞቹ አስመጪዎች ከአዲስ አበባ ውጪ መሆናቸው ለቁጥጥርና ክትትል ችግር እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የቁጥጥር ስራን የሚያግዝ የመሸጫ ዋጋ ማዕቀፍ ማስቀመጥም እንደመፍትሄ ሲጠቀስ፤ ከዚህ ያለፉትን ደግሞ የንግድ ፍቃድ አስከመቀማት የሚደርስ ቅጣት ይጣላል ተብሏል፡፡

የሃገር ውስጥ የፈሳሽ ዘይት አምራቾች የግብዓት እጥረት መኖሩን ሲያነሱ፤ ከውጭ ዘይት የሚያሥመጡት ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘይት ዋጋ መጨመሩን እንደምክንያት አንስተዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!