ቢዝነስ

ኢትዮጵያ በ38ኛው የካርቱም ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢትና ባዛር እየተካፈለች ነው

By Tibebu Kebede

January 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ38ኛው የካርቱም ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢትና ባዛር ላይ እየተካፈለች ነው።

በንግድ ትርኢትና ባዛሩ ላይ መቀመጫቸውን ሱዳን ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ኤምባሲዎችና ኩባንያዎች ተሳታፊዎች ናቸው።

ባዛሩ የኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ንግድ፣ ኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ሃብቶች ለማስተዋወቅ ይረዳል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም “ራይዚንግ ኢትዮጵያ” በሚል ሃሽታግ ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ የተያዘውን ዘመቻ ለማሳወቅ ያግዛልም ነው የተባለው።

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ አነስተኛ መካከለኛ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥርላቸውም ተገልጿል።

ለሁለት ሳምንት የሚቆየው የንግድ ትርኢትና ባዛር በሃገራቱ መካከል የንግድ ትስስስርን በማጠናከር የቢዝነስና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያግዛል መባሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!