የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከመተከል ከተፈናቀሉ ተጎጂዎች ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

January 23, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከመተከል የተፈናቀሉ እና በቻግኒ ራንች መጠለያ ጣቢያ ከተጠለሉ ተጎጂዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ተስፋዬ ቤልጅጌ፣ የኮማንድ ፖስቱ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ፣ አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

“መንግሥትን የሚረዳ ሠራተኛ ገበሬ የዕለት ጉርሻ እየጠየቀ ሊቀጥል አይገባም” ያሉት ተፈናቃዮቹ፣ መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጠይቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!