የሀገር ውስጥ ዜና

የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ

By Meseret Awoke

January 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያዩ የትምህርት መርሀግብሮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል፡፡

በዚህም የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 344 አስመርቋል፡፡

ዛሬ ከተመረቁት መሀል 1ሺህ 330ዎቹ ሴቶች ናቸው።

በመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺህ 28፣ በሁለተኛ ዲግሪ 313፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ደግሞ በሦስተኛ ዲግሪ 3 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲም በቡሬ ካምፓስ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 735 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ከተመረቁት ውስጥ 292ቱ ሴቶች ናቸው፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን 480 የህክምና ባለሙያዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

ኮሌጁ ያስመርቃቸው በቅድመ ምረቃ 140 ምሩቃን ሲሆኑ፤ በድህረ ምረቃ ደግሞ 340 ናቸው።

ከተመራቂዎቹ መካከልም 141 ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!