የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓታት 417 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

By Meseret Awoke

January 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 417 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በኢትዮጵያ 5ሺህ 85 የናሙና ምርመራ ተደርጓል።

በዚህም 417 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133ሺህ 298 ደርሷል።

በሌላ በኩል 217 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 118ሸሺህ 730 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!