የሀገር ውስጥ ዜና

ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ሚዲያው እንዲታገል ጥሪ ቀረበ

By Tibebu Kebede

January 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሶማሊ ክልል የመንግሥት ሴክተር መስሪያ ቤቶች የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ።

የክልሉ አስፈፃሚ ቢሮዎች ፣ የዞኖች አስተዳደር እና የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ መሰረት ተገምግመዋል።

የግምገማ ሂደቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡሶማን መርተውታል።

የተጀመሩት ፕሮጀክቶች አፈፃፀምና ሂደት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና በእቅዶች ተካተው የነበሩት ጉዳዮች መተግበራቸው ላይ ሰፊ ግምገማ ተደርጓል።

ዛሬ በግምገማው ማጠናቀቂያ ቀን ላይ የክልሉ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሴክተር፣ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንትና ዲያስፖራ ጉዳዬች ቢሮ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።

በዚህም ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ሚዲያው እንዲታገል ጥሪ ቀርቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!