የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ከሱዳን ጋር የምትደራደረው በቅድሚያ የሱዳን ኃይል የያዘውን መሬት ሲለቅ ነው- አምባሳደር ዲና

By Meseret Awoke

January 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ከሱዳን ጋር ለመደራደር በቅድሚያ የሱዳን ኃይል የያዘውን መሬት ሲለቅ መሆኑን አምባሳደር ዲና አስታወቁ፡፡

ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ከሱዳን ጋር የምትደራደረው በቅድሚያ የሱዳን የጦር ሃይል ድንበር አልፎ የያዘውን የኢትዮጵያ መሬት ሲለቅ ነው የሚል ፅኑ አቋም ያላት መሆኑን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ከብሔራዊ ጥቅም ጋር የተያያዙ የሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዲፕሎማሲያዊ አብይት ክንውኖች ላይ አተኩረዋል።

በሁለቱ አገሮቾ ለሽምግልና እና ድርድር የሚፈልጉ ወገኖችን “እናመሰግናለን” ያሉት አምባሳደር ዲና ድርድሩ የሚጀመረው የሱዳን ወታደራዊ ሃይል የኢትዮጵያን መሬት ሲለቅ ነው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!