የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል 7 ከተሞች ወደ ከተማ አስተዳደርነት አደጉ

By Meseret Awoke

January 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መሥተዳደር ምክር ቤት የ7 ከተሞችን ደረጃ ሽግግር አፅድቋል።

ምክር ቤቱ በአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ተጠንተው የደረጃ ሽግግር እንዲደረግላቸው የቀረቡ 7 ከተሞችን ደረጃ ሽግግር አፅድቋል።

ወደ ከተማነት ያደጉት ቲሊሊ፣ ወገልጤና፣ ሃራ፣ አምደወርቅ፣ ቱለፋ፣ ጨፋሮቢት እና ሰንበቴ ከተሞች ሲሆኑ ሁሉም ከተሞች ከመሪ ማዘጋጃ ወደ ከተማ አስተዳደር ደረጃ ተሸጋግረዋል።

በተጨማሪም 5 ከተሞች ካሉበት ደረጃ ከፍ በማለት ወደ ሪጂኦፖሊታንትነት የማደግ ጥያቄ አቅርበዋል።

ጥያቄውን ያቀረቡት ደብረ ታቦር፣ ወልድያ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን እና ኮምቦልቻ ሲሆኑ መስፈርቱን ሲያሟሉ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅም አብመድ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!