Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በቀጣዩ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር ይወያያል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እንደሚወያይ አስታወቀ።

የውይይቱ ዓላማም የጊዜ ሰሌዳውን ለማዳበር የሚያስችል ግብዓትን መሰብሰብ መሆኑንም ነው ያመለከተው።

የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ከባለድርሻ አካላቱ ጋር በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ውይይት ተደርጎ በሚገኘው ግብዓት ከዳበረ በኋላ ይፋ ይሆናል።

የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የቀጣዩ ብሄራዊ ምርጫ መረጃ ደርሶናል በሚል ያወጡት ዘገባ ትክክል አለመሆኑንም ቦርዱ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.