የሀገር ውስጥ ዜና

ሶስት መቶ አርባ አንድ ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Meseret Awoke

January 31, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሶስት መቶ አርባ አንድ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

76 ህፃናትን ጨምሮ ሶስት መቶ አርባ አንድ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት ህፃናት ውጭ 265ቱ ሴቶች ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!