የሀገር ውስጥ ዜና

በአንድ ሳምንት ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሚኒስቴሩ ገለጸ

By Meseret Awoke

January 31, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከጥር 14 እስከ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 64,025,470.75 ብር ግምተዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ወደ ሀገር ለማስገባት እና ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድ ግምታዊ ዋጋ 48,382,510.75 ብር ሲሆን 17,642,960 ብር የሚገመት የወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ ኬላዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል መድኃኒት፣ የምግብ ምርቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የትምባሆ ውጤቶች፣ አደንዛዥ ዕፆች እና የኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች ይገኙበታል፡፡

ሚኒስቴሩ ዕቃዎቹን በጉምሩክ ሰራተኞች እና በፀጥታ አካላት እንዲሁም በህብረተሰቡ ርብርብ መያዝ ተችሏል ብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!