የሀገር ውስጥ ዜና

የአገው ፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በእንጅባራ ከተማ ተከበረ

By Meseret Awoke

January 31, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአገው ፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በእንጅባራ ከተማ ተከበረ።

በበዓሉ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፥የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅ ሰሙ ማሞ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የማህበሩ አባላት እና ተወላጆች ተገኝተዋል።

የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር የአገው አባቶች ከሌሎች አባት አርበኞች ጋር በመተባበር የጣልያንን ወራሪ ጦር ዓድዋ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን ለመዘከር በየዓመቱ ጥር 23 በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚከበር በዓል ነው፡፡

ማኅበሩ በ1932 ዓ.ም ከ30 በማይበልጡ አባላት ነበር የተመሰረተው፤ በአሁኑ ወቅት ከ53 ሺህ በላይ አባላት አሉት፡፡

“ባህላችን ለአብሮነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ 81ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ በእንጅባራ ከተማ ተከብሯል።

የጀግንነት፣ የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የፍቅር ተምሳሌት የሆነው የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በእንጅባራ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደተከበረ አብመድ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!