Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ በነገው መደበኛ ጉባኤው የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

በስብሰባውም የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ነው የተነገረው፡፡

ምክር ቤቱ የፌዴራል ዳኝነት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራም ነው የተጠቆመው፡፡

እንዲሁም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.