Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ኢኳቶሪያል ጊኒ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማላቦ አለም አቀፍ አውሮፕላን ሲደርሱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቶዶር ኦቢያንግ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ዶክተር ዐቢይ በቆይታቸው ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እና በተለያዩ ጉዳዮች ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በትናትናው ዕለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝ ጊኒ ኮናክሬ መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በቆይታቸውም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር የተወያዩ ሲሆን የኮናክሬን ወደብ ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢኳቶሪያል ጊኒ ጉብታቸውን ሲያጠናቀቁ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናሉ፡፡

በአላዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.