የሀገር ውስጥ ዜና

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ተገቢ በሆነ መልኩ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እንዲቀጥል ኢትዮጵያ አሳስባለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

By Tibebu Kebede

February 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ  የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በተመለከተ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው በትግራይ ክልል የሠብአዊ አቅርቦቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

የደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርነት ተጠናቆ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሊቀመንበርነቱን የምትረከብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ  ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጉብኝት ማድረጋቸው በመግለጫው ተነስቷል።

ፕሬዚዳንቷ በጉብኝታቸው የግድቡ የድርድር ጉዳይ ተገቢ በሆነ መልኩ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እንዲቀጥል ማሳሰባቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር  ደቡብ አፍሪካ ግድቡን አስመልክቶ ጉዳዩን ለያዘችበት መንገድ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይን በተመለከተም አውደ ጥናት መካሄዱን ያነሱት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ በሠላም አቋሟ መቀጠሏን  አንስተዋል።

በለይኩን ዓለም

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!