Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጊኒ ሪፐብሊክ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የትብብር ስራዎችን ለማስጀመር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ የትብብር ሥራዎችን ለማስጀመር ተስማምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጊኒ ሪፐብሊክ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት ትናንት ማምሻውን የተለያዩ ስምምነቶችን በመፈጸም አጠናቀዋል።

በዚህ መሰረትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ከፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ጋር በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና ኢነርጂ ዙሪያ የትብብር ሥራዎችን ማስጀመር የሚያስችሉ ወሳኝ ስምምነቶችን መፈጸማቸው ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ በነበራቸው ቆይታ ከናይጄሪያዋ ካዱና ግዛት ሀገረ ገዢ ኤል ሩፋይ እና ከናይጄሪያው ስመጥር የንግድ ሰው ቶኒ ኦሉሜሉ ጋርም ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ በማበብ ላይ ባሉ በርካታ ዘርፎች ላይ መሳተፍ በሚያስችሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ መምከራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.