Fana: At a Speed of Life!

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ብልጽግና ፓርቲና መንግስት በቀጣይ ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲሰሩ ያነሳሳ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ብልጽግና ፓርቲና መንግስት በቀጣይ ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲሰሩ ያነሳሳ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በኦሮሚያ ክልል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ለወጡ የክልሉ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ከሁሉም በላይ ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት በሰላማዊ መንገድ ይህን ሰልፍ አዘጋጅቶ እስከመጨረሻው ያለምንም ችግር በመጠናቀቁ የላቀ ምስጋና አለኝ ብለዋል፡፡

በተለይም የፀጥታ አካላትና ወጣቶች እንዲሁም የሚዲያ አካላት ሰልፉ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በክልሉ ትናንትና ዛሬ በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ያለምን ችግር መጠናቀቃቸው አራት ትልቅ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ናቸው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

በዚህም የክልሉ ህዝብ ጥቅሙን እና መብቱን በደንብ የተረዳ መሆኑን፣ ሰልፉ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የብልጽግና አመራር እስካሁን ያስመዘገቡትን ድል ለማመስገን፣ ለመደገፍና በቀጣይ ለሚያከናውኑት ስራ ህዝቡ ያለውን ድጋፍ ያሳየበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም ሰልፉ ጁንታው በመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት ህዝቡ ቁጭቱን የገለጸበት መሆኑን ያሳየ እንደነበርም አስረድተዋል፡፡

የታየው የህዝቡ ሞራልና መነሳሳት ብልጽግና ፓርቲና መንግስት በቀጣይ ስራዎቻቸውን የበለጠ እንዲሰሩ ያነሳሳ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.