Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራውን አውከዋል ባላቸው 51 ተማሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራውን አውከዋል ባላቸው 51 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው ትምህርት እንዲስተጓጎል ፍላጎት ያላቸው እና ሁኔታዎችን በመጠቀም ችግር የፈጠሩ ተማሪዎችን በመለየት እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

በዚህም መሰረት በ20 ተማሪዎች ላይ ከ1 አመት ሙሉ በሙሉ ከትምህርት መርሃ ግብር እስከ ማገድ የደረሰ እርምጃ ሲወሰድ፥ ለ31 ተማሪዎች ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አስታውቋል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ባደረገው ሰፊ ግምገማ 28 የጥበቃ አባላትን በጡረታ እና 29 የሚሆኑትን ደግሞ ከጥበቃ ስራ ማሰናበቱንም ነው የገለጸው።

ዩኒቨርሲቲው ተልዕኮውን ለማሳካት በተለያዩ የአስተዳደር ደረጃዎች ላይ ያሉ ሃላፊዎችን በአዳዲስ ሰዎች በመተካት ላይ መሆኑንም ጠቅሷል።

በዚህም ከተቋማዊ ለውጥ ሂደቱ ጋር በተገናኘ በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ዙሪያ የምክትል ፕሬዚዳንት እና የ3 ዳይሬክተሮች እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የ3 ሃላፊዎችን ለውጥ ማድረጉን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.