ኬንያ በላሙ ወደብ ሰዓት እላፊ አወጀች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ አልሸባብ በላሙ ወደብ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ሰዓት እላፊ ማወጇ ተሰምቷል።
አልሸባብ በቅርቡ ላሙ በሚገኘው የኬንያና አሜሪካ ጥምር ጦር ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል።
የሽብር ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት ሶስት የአሜሪካ ወታደሮች ህይወት ማለፉን ተከትሎም የኬንያ መንግስት በላሙ ወደብ የሰዓት እላፊ ማወጁን አስታውቋል።
በአካባቢው ላልተወሰነ ጊዜ የተጣለው ይህ የሰዓት እላፊ ገደብ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋቱ 10 ሰዓት ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተመላክቷል።
ይህም የፀጥታ አካላት በአካባቢው ሊፈጸሙ የሚችሉ የሽብር ጥቃቶችን ቀድመው ለመለየትና ለመቆጣጠር ያስችላቸዋል ተብሏል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ