Fana: At a Speed of Life!

በአዋሽ ተፋሰስ ቆላማ አካባቢዎች የቆላ ስንዴ ልማት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዋሽ ተፋሰስ ቆላማ አካባቢዎች የቆላ ስንዴ ልማት እየተካሄደ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በተፋሰሱ ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የመስኖ የቆላ ስንዴ ልማት እየተካሄደ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 4 ሺህ ሄክታር የሚሆነው መሬት ለአካባቢው በሚሆን ምርጥ የስንዴ ዘር የተሸፈነ ነው።

ከመጭው የካቲት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ምርት መሰብሰብ እንደሚጀመርም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተፋሰሱ በኦሮሚያና በአፋር ክልሎች በሚገኙ የአርሶ አደሮች፣ የአርብቶ አደሮች፣ የባለሀብቶችና የግብርና ምርምር ይዞታ በሆኑ መሬቶች ላይ ነው የመስኖ ልማቱ እየተካሄደ ያለው።

የቆላ ስንዴ ልማት ማስተዋወቅና ማስፋፋት ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሃገር ውስጥ አምርቶ ለመሸፈን አማራጭ ነው መባሉን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.