Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በሃገራቱ መካከል ያለው ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በባለብዙ ወገን በብዙ አጀንዳዎች ላይ ተደጋግፈው እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነት በመዋጋት በኩል ኢትዮጵያ እያበረከተች ላለው የጎላ ሚና የቱርክ ድጋፍ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋልዋል፡፡

በትግራይ ከልል ከተወሰደው ህግን የማስከበር ዘመቻ ጋር ተያይዞ የቱርክ መንግስት ሉዓላዊነትን በማክበር ለወሰደው አቋም አድንቀው፤ በአሁኑ ጊዜ መንግስት የሰብአዊ ዕርዳታ በማድረስ መልሶ በማቋቋምና ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በክልሉም ከ26 የሚበልጡ የተመድና የዓለም አቀፍ ሰብአዊ ዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ተሰማርተው ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተቃራኒ መንግስት ዕርዳታ ተደራሽነት እንደከለከለ የሀሰት መረጃ የሚያሰራጩ አካላት መኖራቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡

ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ባለሃብቶች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት በፌደራል ደረጃ የተቋቋመ ኮሚቴ መኖሩንም አስረድተዋል፡፡

አቶ ደመቀ የቱርክ መንግስት ሽብርተኞች ይደግፋሉ የተባሉ ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር በኩል መረጃው የሚጣራ መሆኑን ከቱርክ ጋር በንግድና በኢንቨስትመንት በተጠናከረ መልኩ ለመሥራት ትኩረት እንደሚደረግም አብራርተዋል፡፡

በቅርቡ በቱርክ በሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት ወቅት ከመሪዎች ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚደረግ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ለቱርክ ባለሀብቶች ከግብር እና መብራት ጋር በተያያዘ እየደረሰ ስላለው ችግር በቱርክ መንግስት ሽብርተኞችን ይደግፋሉ ተብለው በተፈረጁ ተቋማት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ፣ በትግራይ ክልል የተወሰደውን እርምጃ እንደሚረዱ እንዲሁም በትግራይ ክልል መንግስት ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት ዕርዳታ ለመስጠት ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች በቱርክ መኖራቸውን አስረድተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.