Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን የቀድሞውን ምክትል ፕሬዚዳንት በቁጥጥር ስር አዋለች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ምክትል ሃሳቦ ሃመድ አብደራህማን በቁጥጥር ስር አዋለች፡፡

የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከሰሞኑ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ከተከሰተውና እየተባባሰ ከመጣው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት ያሏቸውን ግለሰቦች እያደኑ ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የቀድሞውን ምክትል ፕሬዚዳንት እና ደጋፊዎች ናቸው የተባሉ አካላትን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሰልፈኞች ለተቃውሞ አደባባይ እንዲወጡ አስተባብረዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው የተነገረው፡፡

ህዝባዊ ተቃውሞው በተስፋፋበቸው ግዛቶች የንብረት ውድመትና ዘረፋ በስፋት እንደሚስተዋል የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ያመላክታል፡፡

በሃገራቱ የተስፋፋውን ተቃውሞ ተከትሎ በሰባት ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.