Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 3 ወራት በተለያዩ ጊዜያት በትግራይ ክልል ተገኝተው ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች አለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 75 አባላት ፈቃድ ተሰጥቷል-የሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 3 ወራት በተለያዩ ጊዜያት በትግራይ ክልል ተገኝተው ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች አለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 75 አባላት ፈቃድ መስጠቱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በትግራይ ክልል የሰላም ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ በክልሉ ላለፋት 3 ወራት የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዩ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ26 በላይ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በጥምረት የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ተግባራትን ለማገዝ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲደረግ መቆየቱን አንስቷል፡፡
ባለፉት 3 ወራት በተለያዩ ጊዜያት በትግራይ ክልል ተገኝተው ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች አለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 75 አባላት ፈቃድ መስጠቱን ገልጿል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት በአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል በምክትል ሰብሳቢነት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፉንና የመልሶ ማቋቋም ሂደቱን የማስተባበር ሂደቱን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እያስተባባረ እንደሚገኝ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.