Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን 120 ሽፍቶች እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ 120 ሽፍቶች በሠላማዊ መንገድ በመተከል ዞን ለተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል እጃቸውን ሰጡ።

የምዕራብ ዕዝ ህብረት ዘመቻ ሃላፊ ተወካይ ኮሎኔል ፋሲል ይግዛው ÷ሽፍቶቹ በከሰረው በህወሓት ጁንታ ቡድን የሀሰት ትርክት ጫካ ገብተው እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም የመረጣችሁት አማራጭ ስህተት እንደሆነ አውቃችሁ በሠላማዊ መንገድ መምጣታችሁ የሚደገፍ ነው ÷አሁን በዞኑ ውስጥ በሚደረገው የሠላም እና የልማት እንቅስቃሴ ሚናችሁን መጫወት አለባችሁ ብለዋል ፡፡

በጫካ የነበሩ የሽፍታው ቡድን አባላት በሠላማዊ መንገድ እንዲገቡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ እንዲሁም ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ እንደሰሩ ተገልጿል።

በጫካ ሽፍቶችን ሲመራ የነበረው ላቀው ደረጄ እና አዲሱ ፈጠነ በሰጡት አስተያየት፣ የህወሓት ቡድን መቐለ በመጥራት ሲያሰለጥናቸው እንደነበረ ተናግረው፣ አሁን ግን በአካባቢያቸው በተጀመረው የሠላም እና የልማት እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ለመሆን እጃቸውን መስጠታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details…
በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.