Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የአድዋ ድል በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡
የክልሉ የሰራተኞችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊና የአድዋ ድል በዓል አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ሙልነሽ አበበና የክልሉ ባህልናቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ እና የበዓሉ ኮማቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ሙሉቀን አዳነ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫው የዘንድሮው 125ኛውን የአድዋ ድል በዓልን በልዩ ሁኔታ ከክልል እስከ ወረዳ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ዶክተር ሙልነሽ ገልፀዋል ፡፡
የዘንድሮው የአድዋ ድል በዓል ልዩ የሚደረገውም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሀገራዊ አርማ ወጥቶለት በእያንዳንዱ ክልል በደመቀ ሁኔታ የሚከበር በመሆኑ እንዲሁም በዓሉ በድምቀት እንዳይከበር እና ታሪኩ እንዳይነገር ሲያደርግ የነበረው የህዋሃት የጥፋት ቡድን ድል የተደረገበት መሆኑ ነው ብለዋል ፡፡
የአድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን የአፍሪካ ሀገራት የነፃነት ተምሳሌት እንዲሁም የነጭን የሀሳብ የበላይነት በማሸነፍ የአለም ፖለቲካን የቀየረ ታሪክ ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም ይህን የአድዋ ድል ታሪክ ከቅድመ እስከ ድህረ ታሪክ ያለውን ክዋኔዎች የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ ኪነ ጥበብ ትሪኢቶችና በታሪክ ተመራማሪዎች ጥናታዊ ስነፅሁፍ ይከበራል ብለዋል፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.