የሀገር ውስጥ ዜና

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ት/ቤት የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃን አስመረቀ

By Tibebu Kebede

February 13, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ጦሯን ለዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ማዝመቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃን ዛሬ አስመርቋል፡፡

ሕግን በማስከበር እና በህልውና ዘመቻ ላይ የቆየው የመከላከያ ሠራዊት ፣ የጎረቤት ሀገርን ሠላም ለማስፈን ወደ ጁባ ለመዝመት ስልጠናውን አጠናቆ ተመርቋል፡፡

ከምረቃው በኋላም ላይ የስራ መመሪያ መቀበላቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!