Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከወጣቶች ጋር በመሆን በከተማዋ በግንባታ ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከወጣቶች ጋር በመሆን በከተማዋ በግንባታ ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሓላፊ አቶ መለሰ ዓለሙን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በመሆን የመስቀል አደባባይ፣ የታላቁ ቤተ መንግሥት ተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የታላቁ ቤተ መጽሐፍት እና የአድዋ ሙዚየም 00 ኪ.ሜ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች እየተገነቡ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ውስብስብ ችግሮችን በተቀናጀ መልኩ መፍትሔ መስጠት እንደሚቻል የሚያረጋግጡ መሆናቸውን አቶ መለሰ ዓለሙ ተናግረዋል።

በአድዋ ስም እየተገነባ የሚገኘው ፕሮጀክት ታሪክን ይዘክራሉ ያሉት አቶ መለሰ ሌሎቹ ፕሮጀክቶችም ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ሽግግር የሚደረግባቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ እና የለውጡ ፍሬ መሆናቸውን ሓላፊው አስገንዝበዋል።

ለአመራሮቹ ስለፕሮጀክቶቹ ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልልቅ ፕሮጀክቶች ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሺመልስ እሸቱ ÷ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በከተማዋ የሚስተዋለውን የፓርኪንግ ችግር ከማቃለሉ ባለፈ ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ስፖርታዊ ክንዋኔዎችን በተመቸ ሁኔታ ያስተናግዳል ብለዋል።

በተጨማሪም የታላቁ ቤተ መንግሥት ተሽከርካሪ ማቆሚያ ፕሮጀክት ከአንድ ሺህ በላይ መኪና ማስቆም የሚችሉ አራት ወለሎች እንዳሉት ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታላቁ ቤተ መጽሐፍት ቤት በአንድ ጊዜ ከሁለት ሺህ በላይ ተጠቃሚ የሚያስተናግድ ሲሆን፣ ካፍቴሪያ እና ሱቆችም የተካተቱበት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የአድዋ ሙዚየም 00 ኪ.ሜ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህንፃ እና ከሌሎች በዙሪያው ካሉ ታሪካዊ ህንፃዎች ጋር ተናብቦ የአድዋን ታሪክ በሚያንፀባርቅ መልኩ እየተገነባ እንደሚገኝ ኢንጂነር ሽመልስ  ገልጸዋል።

አጠቃላይ ፕሮጀክቶቹ 80 በመቶ ግንባታቸው መጠናቀቁን ያስረዱት ኢንጂነር ሽመልስ ከፊሎቹ በዚህ ዓመት የሚጠናቀቁ ሲሆን÷ ቀሪዎቹ ደግሞ በቀጣይ ዓመት በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚጠናቀቁ መግለጻቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.