Fana: At a Speed of Life!

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የሚኒስቴሩ አመራር የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታልን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመሩት የጤና ሚኒስቴር አመራሮች የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል ።

በጉብኝታቸው ሆስፒታሉ ለአካባቢው ማህበረሰብ እየሰጠ ያለውን አጠቃላይ የጤና አገልግሎት ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ከሆስፒታሉ ስራ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር ከህክምና ግብዓት እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ያሉባቸውን ችግሮች በዝርዝር ተወያይተዋል።

የአርባምንጭ ሆስፒታል በ1961 ዓ.ም በመጀመሪያ ሆስፒታልነት ስራውን የጀመረ ሲሆን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አጠቃላይ ሆስፒታል ማደጉንና አጎራባች ዞኖችን እና የጋሞ ዞንን ጨምሮ ለአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ ለጎብኝዎቹ አስረድተዋል።

ሆስፒታሉ ባለፉት አመታት ያሳየው ለውጥ በጣም የሚበረታታ መሆኑ ተመልክተዋል።

በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ 24 ሆስፒታሎች የጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማሳደግ እየተተገበረ ያለውን “ያገባኛል” ፕሮግራም ያስጀመሩ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሆስፒታሎች ያለባቸውን ችግር ለይተው አገልግሎታቸውን እንድያዘምኑ የሚያግዝ እንደሆነ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ተገልጻል።

የጤና ሚኒስቴር ፣የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንድሁም ከተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በያገባኛል ፕሮግራም ላይ የተዘጋጀውን ጋላሪ ተገኝተው ከጎበኙ በኋላ የፕሮግራሙ ስኬት እና ተያያዥ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.