Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ኑክቴክ ኩባንያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ኑክቴክ ኩባንያ ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ መግባታቸው ተገለፀ።

ለዑኩ በጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ መተከል ባለበት ማሽኖች ዙሪያ ስራ ለመጀመር አዲስ አበባ መግባቱን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ልዑካን ቡድኑ የጉምሩክ ፍተሻ ጣቢያዎች በዘመናዊ ፍተሻ መሳሪያዎች መተካት በሚቻልበት ሁኔታ ዝርዝር ስራዎች ላይ ከገቢዎች ሚኒስቴርና ከጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዝርዝር የጋራ እቅድ በፍጥነት ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የቻይና ኑክቴክ ኩባንያ ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ከዚህ ቀደም በቻይና ጉምሩክ እና በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መካከል ተደርጎ የነበረውን ስምምነት መሰረት መሆኑም ታውቋል።

በገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተመራ ልኡክ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር በቻይና ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።

በጉብኝቱ ወቅትም ገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከቻይና የጉሙሩክ አስተዳደር ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ህገ ወጥ የንግድ ስርዓትን፣ የዕፅ ዝውውርን ለመቆጣጠር እንዲሁም የጉሙሩክ ስርዓትን ለማዘመንና የጉሙሩክ መረጃዎችን ለመለዋወጥ አንድ የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲዋቀር መደረጉ ተገልጿል።

የቴክኒክ ኮሚቴ ቡድኑ አዲስ አበባ በመምጣት ከኢትዮጵያ ቡድን ጋር የኢትዮጵያን የጉሙሩክ አገልግሎት አሰጣጥ የሚጎበኝ መሆኑ መገለፁም ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም የተለያዩ የቴክኖሎጂ አገልግሎት ድጋፎችን ለኢትዮጵያ ጉሙሩክ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፥ ለጉሙሩክ አገልግሎት ሰራተኞች የተለያዩ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥም በወቅቱ ተገልጿል።

አሁን ወደ አዲስ አበባ የመጣው ልኡካን ቡድንም በስምምነቱ መሰረት በጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ መተከል ባለበት ማሽኖች ዙሪያ ስራ ለመጀመር እንደሆነ ነው የተገለፀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.